Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ይህ ምን አይነት የተመሰቃቀለ ነገር ነው። እንዴት የሚያስጨንቅ ጨለማ ነው እባክህ። አይ ሥ ሯጮ ኝ ሱረቱል አልኢስራ «ባሮቼ በእነሱ ላይ ፈጽሞ ላንተ ስልጣን የለህም መጠጊያም በጌታህ በቃ» ውድ ወንድሜ እስኪ አሁንም ልጠይቅ በእነዚህ ከላይ ባነበብካቸው የቁርአን አንቀጾች ላይ እንደ ሜታየው ሰይጣን የአላህን ባሮች እንዳይነካ ታዞ ከገነት ወጥቷል እርሱም ቢሆን በዚህ ጉዳይ አምኖበት እነርሱን ላይነካ ሌሎቹን ግን ሊያጠማቸው ዝቶ ከአላህ ፊት ወጥቷል እንዲህ ከሆነ ታዲያ ሰይጣን ነቢዩ ሙሐመድንና መላውን ሙስሊም ማሕበረሰብ ከመንካት አልፎ በልባቸው ውስጥ ተንሰራፍቶ በመኖር አመራር በመስጠት ላይ ይገኛል እንዲህ እየሆነ ያለው ነቢዩ ሙሐመድና ሙስሊሙ ማሕበረሰብ የማን ባሪያዎች ቢሆኑ ነው። ሰይጣን የተፈቀደለት የራሱ በሆኑት ላይ ብቻ ከሆነ እናንተ ሁላችሁ የሰይጣን ናችሁ ማለት ነው። ወደሚለው ጥያቄህ ልመለስ ውድ ወንሜ መጽሐፍ ቅዱስን ያንብቡ ወደ እውነተኛ ቤተክርስቲያን በመሄድ በዛ ሕብረት ያድርጉ ለመንፈሳዊ ሕይወት እድገት አስፈላጊ ነው ጌታ በነገር ሁሉ ይባርከዎት።
የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ነቢዩ ሙሐመድም ስለእራሳቸው ፍጹም ሰው ነኝ የአላሀን ሕግጋት በትክክል ፈጽሜአለሁ ጀነት ለመግባቴም ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለኝም በማለት አንድም ቦታ አልተናገሩም ይልቁን ስለ ኃጢአታቸው በቀን ሰባ ጊዜ ንስሃ ይገቡ እንደነበር በሐዲሳቸው ተዘግቧል ምልባት ሁሌ እንደሚባለው አላህ መሐሪ ስለሆነ በምህረቱ ጀነት ያስገባኛል ትለኝ ይሆናል ሆኖም ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ሕግ በባህሪው ፍጹም ሆኖ ያልተገኘን ሰው መቅጣት እንጂ መማር አያውቅም አላህ ለነቢዩ የሰጠው ደግሞ ሕግ ነው እንደ እስልምና አስተምህሮ የሰው ፍጻሜ ከመወለዱ ወይንም ከመፈጠሩ በፊት በአላህ የተወሰነ ስለሆነ ውሳኔውን ሊያጥፈው አይቻልም ሊያጥፈው ይችላል ከተባለ ከማንነቱ ጋር ይጣረሳል አላህ በባህሪው እራሱን ሊጣረስ የሚችል አምላክ አይደለም ታዲያ ሌላ ምን ቢያደርግ ከዘለአለም ሞት መዳን ይቻላል ብለህ ታስባለህ። የአላህ መልእክተኛ ሆይ። አላህ እንዲህ አይነት የአምላክንና የሰው ልጆችን የፍትህ ትርጉም ሊያሟላ የማይችል የፍትህ መጓደል በሰው ልጆች ላይ ይፈጽማል ተብሎ አይታመንም ይህ የቀዷ ወቀድር አስተሳሰብ የአላህን የፍትህ አምላክነት ይጻረራል በመባሉ እስልምናን ከሁለት መክፈሉን ሳትሰማ የምትቀር አይመስለኝም የአላህን ፍትሀዊ አምላክነት የሚጻረር እንዲህ አይነት የኢማን አንቀጽ አንቀበልም በማለታቸው በርካታ ሙስሊሞች በሌሎች ሙስሊም ወንድሞቻቸው ተገድለዋል አላህ ሰዎች መልካም ሥራንና ኃጢአት እንዲሠሩ ቀድሞ የጻፈባቸው ከሆነ እንዲሁም መልካምም ሆነ ክፉ እንዲሆንባቸው የጻፈባቸው እራሱ ከሆነ በምድር ላይ ያለው የመልካምና የክፉ የኃጢአትና የጽድቅ ሥራ ሁሉ ምንጪ እራሱ ነው ማለት ነው ታዲያ የሰውን ልጆች ለማሳት ዝቶ አላህም ፈቅዶለት ከገነት የወጣው የሰይጣን የሥራ ድርሻ ምንድን ነው። ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ ቀድር መሰረት እንደሚከናወን የሚታመን ከሆነ አዳም እንደተናገረው ኃጢአት የሚደረገው በአላህ ስለተወሰነ እንጂ ሰይጣን የነገሮቹ ምንጭ ስለሆነ አይደለም ወደሚል መደምደሚያ ይወስደናል ታዲያ የሰው ልጆች ጠላት መባል ያለበት ሰይጣን ወይንስ አላህ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን አላህ ከዚህ ውጭ የሆነ አምላክ እንደሆነ ያስተምራል እኔም የማምነው ያንን ነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አላህ ከሚናገረው እስኪ ትንሽ ላስነብብህ ኛ የዮሐንስ መልእክት በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ሰይጣን የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት እንደሆነ ቁርአን ይናገራል ታዲያ የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት የሆነው ሰይጣን በውስጡ እንዳለበት እርሱን የሚከተሉትም በአጠቃላይ ሰይጣን በልባቸው እንዳለባቸው የሚያምን ነቢይ የአላህ መልእክተኛ ነው ብለህ ታምናለህ። እስኪ ሌላም ሐዲስ ላስነብባችሁ ኡመር ኢብን ኸታብ በእምነቱ ጠንካራ በአቂዳ ጽኑ የሆነና ዲኑን በደንብ የሚጠብቅ ሰው ነበር እርሱ አላህ የመደበበትን ሰይጣን ተጽእኖ በማድረግ ማስለም አልቻለም ነገር ግን አላማው እንዲፈራው ማድረግ ነበር የአላህ መልእክተኛ ሲናገሩ አማኞች ከአላህ የተመደበባቸውን ሰይጣን ማስለም በጉዚቸው ላይ ያለን ትልቅ ተራራ እንደመውጣት ይቆጠራል አቡ ሁሬይራ የተናገረው ሐዲስ « ወንድሜ እስኪ ደግሜ ልጠይቅህ ነቢዩ እንዳሉት በአንተ ልብ ውስጥ አብሮ የሚኖር የሚመክር ስራህን የሚያጣድፍ ሰይጣን እንዳለብህ ፍዕ ታምናለህ። ሰይጣን ማን ነው። « ሰይጣን በሱረቱል አልሒጅር ሳይ ፍጹም የሆኑትን የአላህ ባሮች እንደማይነካ ለአላህ ቃል ገብቷል በዚሁ ቃል መሰረት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንና እናቱን ማርያምን መንካት እንዳልቻለ በሐዲሱ ተገልጾ ይገኛል በአንጻሩ ነቢዩ ሙሐመድ ደግሞ በልባቸው ሰይጣን እንዳለባቸው አምነዋል ጌታ ኢየሱስ ማርያምና ነቢዩ ሙሐመድ የአላህ ባሮች ከሆኑ በመካከላቸው ይህ ልዩነት ለምን ተፈጠረ። ሰይጣን በልባቸው የሚኖር ሁሉ የሰይጣን ባሪያዎች ናቸው ስለዚህ ከእርሱ ጋር ወደ ገሃነም ይሄዳሉ እንጂ ወደ ገነት አይገቡም ይህንን ያልኩት እኔ ሳልሆን ቁርአን እራሱ ነው ሱረቱል ቧድ ከአንተና ከእነርሱ ውስጥ ከተከተሌህ ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» የተከበሩ ውድ አንባቢ ውዱን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በእምነት በመከተል ጎዳና ላይ ግን እንዲህ አይደለም ነቢዩ ሙሐመድ ሳሄህ በሆነው ሐዲስ ሳሂህ አልቡኻሪ ቀጥሎ በተገለጸው መልኩ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል የነቢዩን ንግግር የምጠቅሰው ምን እንዳሉ ለመግለጽ ያህል እንጂ በእርሳቸው ላይ እምነት ስላለኝ አይደለም ምስክርነታቸው እንዲህ የሚል ነው ሳሂህ አልቡኻሪ ቅጽ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ ከማርያም ልጅ ከኢየሱስ በስተቀር የሰው ልጆች በሚወለዱበት ሰዓት ሰይጣን በሁለት እጣቶቹ የሕጻኑን ገላ በሁለቱም ጎኑ ይነካዋል የኢየሱስን ገላ ለመንካት ሞከረ ነገር ግን አልተሳካለትም በእርሱ ፋንታ የእንግዴ ልጁን መሸፈኛ ነካ አቡ ሁሬይራ የተናገሩት ሐዲስ ነው ሳሂህ አልቡኻሪ ቅጽ የአላህ መልእክተኛ ሲናገሩ የሰማሁት ከአዳም ልጆች መካከል ከማርያምና ከልጄ በስተቀር በሰይጣን ሳይነካ የሚወለድ የለም ስለዚህ ሕጻኑ ሲወለድ አምርሮ የሚያለቅሰው በሰይጣን በመነካቱ ምክንያት ነው ሳይድ ቢን አልሙሳኢያብ ከቡ ሁሬይራ ሰምቶ የዘገበው ውድ ወንድሜ እንደ እኔ እምነት የእስልምና ሃይማኖት አላህ የሰው ልጆችን ለማዳን ቀድሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ከገለጠው የደህንነት ጎዳና ይልቅ ትክክለኛ አማራጭ ሊሆን በፍጹም አይችልም ጀነት መግባትህን እርግጠኛ የማያደርግ እምነት አጥፊው ሰይጣን በውስጥህ አለብህ አለብኝ የሚል ንግግሩ ተቀበልኩ ካለው ቃል ጋር የሚጣረስ ነቢይ የሚመራው ሃይማኖት ከአላህ ሊሆን ከቶውን አይችልም አላህ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በገለጠው እውነተኛ የሕይወት መንገድ ከሰይጣን ጋር ትኖራለህ ሳይሆን የሚለው ሰይጣንን ትረግጣለህ በሰይጣን ትመራለህ ሳይሆን በአምላክህ እየተመራህ ሰይጣንን ታሳድዳለህነ ክፉ ሥራውንም ታፈርስበታለህ በኢየሱስ ስምም ሰይጣንን ከሰዎች ውስጥ ታስወጣለህ ታሸንፈዋልህ እንጂ እርሱን መርታት ዳገት ነው አይልም የሉቃስ ወንጌል ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው። የማርቆስ ወንጌል ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ እባቦችን ይይዛሉ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስለመሆንና አለመሆን ሲናገር ሰው በክርስቶስ የተገለጠውን ሕይወት ሲቀበል የእግዚአብሔር ይሆናል ሳይቀበል ደግሞ የሰይጣን ይሆናል ይሳል በአንዴ ሁለቱም ጋር መሆን ግን አይቻልም እንደ ነቢዩ ሙሐመድ ለእግዚአብሔር ተገዛሁ እያለ እንደገና ከሰይጣን ጋር ኑሮ አለ አይልም ሰይጣን በሰው ልብ ውስጥ አብሮ የሚኖር ከሆነ ያ ሰው ገና የሰይጣን እንጂ የአላህ ሊሆን አይችልም ከሰይጣን ጋር እየኖሩ ጀነት መግባት የማይታሰብ ነው አሁን ወደ መጠቅለሉ እንምጣ ለእኔ አላህ በባህሪው ከላይ በቁርአንና በነቢዩ ሙሐመድ ሐዲሳት ውስጥ እንዳየነው አይነት አምላክ አይደለም እርሱ የፍትሕና የጽድቅ አምላክ ነው በአንድ ጎን የክፋት በሌላው የመልካም ነገሮች ምንጭ አይደለም የዘለአለም አምላክ ይቅርና እንዲህ ተለዋዋጭ ባህሪ የሚታይበት ሰው በማሕበረሰቡ ውስጥ እንዴት እንደሚስተናገድ መገመት ትችላለህ በአንድ እራስ ሁለት ምላስ እንደሚባለወው ማለት ነው መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን በግልጽ ይቃወማል እርሱ መልካም አምላክ ስለሆነ የመልካም ነገሮች ምንጭ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው ይለናል ክፋት ሁሉ የሚመነጨው ከሰይጣን ልብ ብቻ ነው ስለዚህ ነቢዩ ሙሐመድም ሆኑ ቁርአን የአላህን ትክክለኛ ማንነት ማሳየት አልቻሉም ካልቻሉ ደግሞ ከአምላካችን የተላኩ መልእክተኞች አይደሉም ወደሚል መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ ያደርጋል እናም እስልምና ለሰው ልጆች የደህንነት አማራጭ መንገድ ሊሆን በፍጹም አይችልም ከአላህ ያልሆነ ደግሞ ከላይ ያነበብከው ሱራ የሚፈጸምበት ቀጥተኛ መንገድ መሆኑን አምናለሁ ውድ አህመድ አላህ እኛን ለማዳን ከፈለገ ኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕት ሳያደርግ ሊያድነን አይችልም ነበር። መንገድ ነኝ አለ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ፈጥሮ በገነት በደስታና በሐሴት እንዲኖር ፈቅዶለት እያለ አታድርግ የተባለውን በማድረጉ ያን ከመሰለ የክብር ሥፍራ ልዩ ከሆነው መኖሪያው በራሱ ስህተት እንዲወጣ ተገዷል ከዛን ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ መንገዱን ይፈልጋል መንገድ ነው ብሎ ባሰበውም ወደዛው በመንጎድ ላይ ነው የሰው ልጆች ወደ መጀመሪያው መኖሪያቸው መመለስ ይፈልጋሉ ይህንን የተረዳው ሰይጣን በውስጣቸው ያለውን የመመለስ ፍላጎት ማጠፋፋትና አስሮ ማስቀመጥ ባይቻለውም አንድ ነገር ማድረግ ግን ተችሎት እናያለን ብዙ የሆኑ ሃይማኖት የሚባሉ መንገዶችን በመገንባት ትክክለኛውን መንገድ እንዳያገኙት ማድረግ ከዛም የአንተ ነው ትክክለኛው እንጂ የእነንትና አይደለም እያለ አንዱን በአንዱ ላይ ማነሳሳትና እርስ በእርስ በማፋጀት ግራ ማጋባት የተዋጣ ሥራ ሆኖለታል ወገኖቸ ልታውቁት የሚገባው የአዳምንና የልጆቹን ወደ ቀደመው ልዩ መኖሪያ መመለሳቸውን እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ ባለብዙ ምህረቱ ጌታ አምላካችን ለእነርሱ ካለው ፍቅር የተነሳ ከእነርሱ በበለጠ ይፈልገዋል ስለዚህ አምላካችን ለዚህ አላማ አንድና ብቸኛ የሆነ መንገድ አዘጋጀ ሰይጣን እነዛን መንገዶች የሠራው ይህ ብቸኛውና ትክክለኛው መንገድ እንዳይታወቅ ለማድረግ ነው አስተዋይ የሆኑና እርሱን የሚፈልጉ ከመንገዶቹ ሁሉ ይህንን መንገድ መለየት ይችላሉ በአምላካችን የተዘጋጀልን ትክክለኛ መንገድ እኔ መንገድ ነኝ ያለው ጌታ ኢየሱስ ነው እርሱም አምላካችን ወደ አዘጋጀልን የዘለአለም መኖሪያ ወደ ገነት የሚያደርሰን ብቸኛውና አማራጭ የሌለው መንገድ ነው እውነት ነኝ አለ መንገድ ብቻ ሳልሆን እርግጠኛ እንድትሆኑ እውነትና እውነተኛ ገነት የማደርስ መንገድ ነኝ አትተራጠሩ አለ ወገኖቸ የምታዩአቸው ሃይማኖት የተባሉት መንገዶች በሙሉ የሰው ልጆች ወደሚናፍቁት የዘላለም መኖሪያቸው የሚያደርሱ እውነተኛ መንገዶች አይደሉም ከነዛ መካከል እስልምና አንዱ ነው ሁሉም አድራሻቸው ገሃነም ነው ጌታ ኢየሱስ ግን እውነተኛ መንገድ ስለሆነ ወደ ናፍቆታችሁ ወደ ገነት የሚያደርስህ የሚያደርስሽ ከአምላካችን የተሰጠ ልዩና ብቸኛ እውነተኛ መንገድ ነው በዚህ እውተኛ መንገድ ላይ የሚጓዙ ሁሉ በመጨረሻው ዘመን በፍጹም አያፍሩም ከኃጢአትና ከዘለአለም ሞት ባርነት ነጻ የሚያወጣ እውነተኛና እውነት የሆነ ብቸኛው መንገድ እርሱ ብቻ ነው ጌታ ኢየሱስ ይህንን እያለ ያለው እንዲሁ አይደለም የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲለያዩ ላደረጋቸው ለኃጢአት ትክክለኛ መፍትሔ ይዞ በመምጣቱ እንጂ እኔ ሕይወት ነኝ አለ በኃጢአት ምክንያት ከአምላኩ ለተለየው ሰው ወደ ዘለአለም መኖሪያው ለመመለስ የሚያስፈልገው ሕይወት ነበር ምክንያቱም አታድርግ የተባለውን ባደረገ ጊዜ ወደ እርሱ የመጣው ሞት ነበርና ኦሪት ዘፍጥረት እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። እንግዲህ ይህንን የሕይወት መንገድ ቢቀበሉ የገነት ነዋሪ መሆንዎትንና ከሥጋ ሞት በኋላ ወደዛው ለመግባትዎት ገና በምድር ላይ እያሉ ፍጹም እርግጠኛ ይሆናሉ ብቸኛው ወደ ገነት የመግቢያ መንገድ ይህ ብቻ ነው አሁን ይህንን የሕይወት ጌታ በማመን ተቀብለው የመንግስተ ሰማይ ወገን ይሁኑ ብዬ እጋብዘዎታለሁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው በዚህ መንገድ ካልሆነ በቀር ወደ አብና ከእርሱ ጋር ለመኖር ወደ ገነት መጓዝና ወደዛ መግባት አይችሉም ዛሬ ወደዚህ ጌታ ሊመጡና ከማንም በላይ ከሚያፈቅርዎት ውድ አምላክዎት ጋር ሊታረቁ ይገባል እኔም እባክዎትን ይታረቁ ብየ እንለምንዎታለሁ ይህንን የሕይወት መንገድ ለመከተልና በእርሱ ለመኖር ፈቃደኛ ከሆኑ የሚከተለውን ጸሎት ይጸልዩ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ለእኔ ስላለህ ፍቅር አመሰግናለሁ እንደምትወደኝ አውቄአለሁ ስለላክልኝ የሕይወት መልእክተኛ ስለ ልጅህ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ ላ ጌታ ኢየሱስ ሆይ በእኔ ኃጢአት ምክንያት መስቀል ላይ ሞተህልኛል አምናለሁ ከሞትም መነሳትህንም አምናለሁ እኔ ኃጢአተኛ ሰው መሆኔን አምናለሁ አሁን ይቅር እንድትለኝ ከበደልም በፈሰሰው ደምህ አጥበህ እንድታነጻኝ እለምንሀለሁ ልጅህ አድርገህ ተቀበለኝ ለአንተ ቀሪ ሕይወቴን ለመገዛት ወስኛለሁ ዓለምንና ሥራውን እንዲሁም ሰይጣንን ክጃለሁ ስለተቀበልከኝ ይቅር ስሳልከኝ ልጅህም ስሳደረግከኝ አመሰግናለሁ እንኳን ደስ ያለዎት።