Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ለምሳሌ በሀገረ እሥራኤል አህዮች እጅግ የሚወደዱ የቤት እንስሳት ነበሩ ነገሥታቱም ካህናቱም ነብያቱም ዘመኑ ዘመነ ሰላም ሲሆን በአህያ ነው በጥንታውያን ግብጾች ዘንድ አህያ የመኳንንትና የነገሥታት ሀብት ማሳያ ነበር የናርማር ወይም የሖር አሃመቃብር እንደሆነ በሚታመነው ቦታ ላይ በተደረገ ቁፋሮ አህዮች ከነገሥታቱ ጋር በክብር ተቀብረው ተገኝተዋል በዚያ ጊዜ አህዮች የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየተመገቡ በቤተ መንግሥቱም እየተሸለሙ ኖረዋል በሌላው ዘመን ደግሞ ይህንን ፈረሶቹ ወስደውታል «ወደኋላ ተመልሰሽ ሁሉን እንስሳት ብታያቸው ታሪካቸው እንደዚሁ ነው ልጄ በዘርሽ አትጨቁኝም በዘርሽም አትጨቆኝም የጭቆና መሠረቱ ጋይልና ሥልጣን ነው አቤልን የገደለውኮ ቃየል ነው የአንድ ማኅፀን ልጆች ናቸውኩ ቃየል አቤልን የገደለው ለጥቅም ሲል ነው እስኪ የሰዎችን ታሪክ እይው አፍሪካውያንኮ በራሳቸው በአፍሪካውያን ይጨቆኑ ነበር ሥልጣን ላይ ያለው ሰው መሰሎቹን ይሰበስብና ሌሎቹን የሀገሩን ልጆች ይጨቁናል መጀመሪያ የገዛ ወገኖቻቸውን ለዐረቦች በባርነት ሲሸጡ የነበሩት የሀገራቸው ሰዎች ነበሩ አፍሪካውያን በባርነት ተሽጠው አሜሪካ ሲሄዱ ደግሞ ነጮቹ ጥቁሮቹን መጨቆን ጀመሩ አየርላንዳውያን በእንግሊዞች መከራቸውን አይተዋል ዓረቦች በዓረቦች ተሰቃይተዋል አየሽ ቤተ መንግሥቱ ላይ ስትቀመጭ ሌላውን ለማግለል ሳጥን ትከፍቻለሸ ከዚያ ሁሉንም በየሳጥኑ ታስቀምጭዋለሽ የእምነት የዘር የመልክ የአካባቢ የቋንቋ ሳጥኖችን ከፍተው ሁሉንም እዚያ ስላስቀመጧቸው ተቀማጮቹ ሳጥኑን እንዳለ ተቀበሉት ማንነታቸውም አደረጉትና ሳጥኑን ለማስቀረት ከመታገል ይልቅ ራሳቸውን ብቻ ከሳጥኑ ለማውጣት ይታገሉ ነበር በሳጥኑ ዛሬ አህዮች ይገቡበታል ነገ ፈረሶች ከነገ ወዲያ ግመሎች ከዚያም በጎች ከዚያም ፍየሎች እየገቡበት ይቀጥላል እኛም ዛሬ ያለሳጥን መኖር ከማንችልበት ዘመን ላይ ደርሰናል እኔን ሲያገኙኝ እንስሳ መሆኔን አይደለም የሚያዩት የትኛው እንስሳ። የዱር ወይስ የቤት። ይቀጥላል የቤት ለጭነት ወይስ ለግልቢያ።ንንአለኝ ብሎ ሲያወራ ሰማሁት አየሽ ሌላን ማግለል ስትፈልጊ የሆነ ነገር ትፈጥሪያለሽ ማቅረብም ስትፈልጊ እንደዚያው ርብዙ ዓይነት ነጻ አውጭዎች አሉ እኔ አሁን የፈረስ ነጻ አውጭ ውስጥ ልግባ ወይስ የአህያ።
የበቅሎዋ ጥያቄ ዲን ዳንኤል ክብረትን አንዲት ግልገል በቅሎ እናቷን እንዲህ ብላ ጠየቀቻት እማዬ እኔ ግን ማነኝ እናቷም ገረማትና አንቺማ በቅሎ ነሽ ግን ለምን ጠየቅሽኝ ግልገሏም ጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ መጀመሪያ ግን አህያ ነበርኩ ወይስ ፈረስ አለቻት እናቲቱም አንገቷን ነቅንቃ እንስሳ ነሽ ልጄ እንስሳ ፈረስም አህያም እንስሳ ነው ስንፈጠር እንስሳ ነበርን የቤት የዱር የሸክም የግልቢያ የእርሻ የሜዳ የንጉሥ የባሪያ የሚለው በኋላ የመጣ ነው አዳምኮ ሲፈጠር ቤት አልነበረውም ስለዚህ የቤት እንስሳ አልነበረም ማለት ነው ሁላችንም ይህቺን ምድር እንደልባችን እንጠቀምባት ነበር ነገር የመጣው በኋላ ነው ለመኖር የሚደረግ ትግል ነው ይህንን አሁን ያለንበትን ሁኔታ የፈጠረው ጓደኛዬ የአንቺ አያቶች ጨቁነውናል አለኝ እንዴት አድርገው ነው የጨቆኑት ለመሆኑስ የአንቺ አያቶች ስንት ናቸው። የዱር ወይስ የቤት። ይቀጥላል የቤት ለጭነት ወይስ ለግልቢያ። ወይስ የበቅሎን አለቻት ግልገሊሏ ርየእንስሳት ነጻ አውጭ ካለ እዚያ ግቢ አንቺ እንስሳ ነሽ የቀረው ከመኖር የመጣ ስም ነው እንስሳት ሁሉ ነጻ ሳይሆኑ በቅሎ ተለይታ ነጻ ልትሆን አትችልም አንድን አካባቢ ብቻውን ንጹሕ ማድረግ አትችይም ምክንቱም ዝንቧ ከወዲያኛው ማዶ ትመጣለችና ከእኛም ወገኖችኮ ሜዳ በመኖራቸው የተነሣ የሜዳፈረስ ተብለው የቀሩ አሉ እኛ ከሰው ተጠግተን የቤት ፈረስ ለመሆን ቻልን የቤት አህዮች አሉ የሜዳ አህዮች ም አሉ የስም ጉዳይ ነው የአኗኗር ጉዳይ ነው በቤተ መንግሥት ከነገሥታት ጋር የሚኖር አንበሳ ነበርኮ የነገሥታቱ ዙፋን እንዲያውም የአንበሳ ቅርጽ ነበረው በዚያው ዘመን ግን ንጉሁው ጫካ ወጥተው ሌላ አንበሳ ገድለው እየተዘፈነላቸው ይመጣሉ ጀርባሽን ለመጋለብ ምቹ ካደረግሽው ምንጊዜም የተሻለ ተወዳጅ ትሆኛለሽ እንግሊዞች ፀፀበዐፀ ዐበ ከ ር ዩኗበባፎ ከከ ዐበ ከዕኗፀ ከ ከዐዕሃኗ በ የምትገለብጠኝን ፈረስ ከምጋልብየምትሸከመኝን አህያ ብጋልብ ይመረጣል ይላሉ ቤት የቀረው ውሻ ዱር ከቀረው ውሻ ጋር በመለያየታቸው ዛሬ አንዱ አንዱን እንደ ጠላት ያባርረዋል ሰው ብልጥ ነው አንዱን ወደ ራሱ አቅርቦ ውሻ አደረገውና ቦቢ እያለ በማቆላመጥ ነጻ የወጣ አስመሰለው ሌላውን ደግሞ ቀበሮ ተኩላ ብሎ ጫካ ተወውና እርሱን መግደል ጀግንነት እንዲሆን አደረገው አሁን ውሾቹ የሠለጠኑና ነጻ የወጡ መስሏቸው ተኩላና ቀበሮ ሲያብርሩ ይኖራሉ አየሽ ጉዳዩ የዘር አይደለም በዘር ከሰው ተኩላ ለውሻ ይቀርበዋል ቀበሮ ይዛመደዋል ጉዳዩ የጥቅም ጉዳይ ነው የመደብ ጉዳይ ነው ከቀበሮውና ከተኩላው መካከል ደግሞ የተወሰነውን ይወስዱና ፓርክ ውስጥ አስገብተው ያለፈለት ያስመስሉታልእርሱም ማግኘት የሚገባውን ሳይሆን ራሱን ከጫካው ኑሮ ጋር ስለሚያነጻጽር ተመስገን እያለ ይኖራል ነጻነት የፍጡር ሀብት ነው ለእነ እገሌ ተብሎ የሚቆረስ አይደለም ጨቋኙም ተጨቋኙም ነጻ ካልወጣ ሙሉ ነጻነት አይገኝም ጨቋኝነት ከአስተሳሰብ ባርነት የሚመጣ ነው ከአመለካከት ድህነት የሚከሰት ነው ሙሉ ነጻነትን ለማግኘት እርሱን ነጻ ማውጣት አለብሽ ካልሆነ ግን ጉዞው አንዱን ጨቋኝ በሌላ ጨቋኝ መተካት ነው የሚሆነው አፍሪካው።