Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

ትምህርተ ሃ፣ሰ፣ታ፣ም.pdf


Advertisement
  • word cloud

ትምህርተ ሃ፣ሰ፣ታ፣ም.pdf
  • Extraction Summary

ይህ ከሆነማ አባባሉ ከእሱ በላይ ስለእሱ አውቃለሁ ማለትም ትክክለኛ ዕውቀት አይሆንም ፍጥረተ ዓለምና ምሥጢረ ተፈጥሮ ሥነ ፍጥረትን ክሥተት ያህል የማያስደንቅ ተአምራዊ ኑሮ ነው ከሚከተለው ጥቅስ ስለፈጣሪው ሠራዒ መጋቢነት እንዲፈጸም ከመደረጉ በቀር የተቀነሰ ወይም የተጨመረ ነገረ ሃይማኖት ትምህርታችን ይህ ምሥጢር ትንሣኤ ሙታን ይባላል ሰው ከፈረሰና ከበሰበሰ በኋላ ይነሣል ስንል እንዲያው በማናውቀው አይደለም። ከዚህም ጋር በግብር ስያሜ ብርሃን ዮሐ ኖላዊ ዮሐ የሕይወት መንገድ ዮሐ አልፋና ኦሜጋ ራዕፅ የባሕርይ አንበሳ ራዕ ረቢ መምህር ዮሐ የእግዚአብሔር በግ ዮሐ ሊቀ ካህናት ዕብ ወዘተ እየተባለ ይጠራል ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በክርስቶስ መቶ ሃያ ቤተሰብእ ወይም ደቀመካሙርት ማለት ሐዋርያት አርድዕት ቅዱሳት አንስት አንድነትና ኅብረት ነው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በወረደበት ዕለት በዓለ ሃምሳን ለማክበር ለተሰበሰበው ሕዝበ በተላለፈው የቅዱስ ጴጥሮስ ቃለ ስብከት ብዙዎች የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ የሐዋ ይህ አንድነት እስከ አስጢፋኖስ ሞት ድረስ እያደገ ከሄደ በኋላ በእስጢፋኖስ ሞት ተበተኑ።

  • Cosine Similarity

ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት ክፍል በየሰንበት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስተማሪያ የተዘጋጀ መስከረም ዓም ርእስ መግቢያ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት መግቢያ የክርስትና እምነት መሠረተ ትምህርት ምሥጢረ ኩነት አምላካዊ ፍጥረተ ዓለምና የፈጣሪ ሠራዒ መጋቢነት የሰው ልጅ ተፈጥሮና ኑሮው ተስፋ ድኅነት ድኅነት ምሥጢረ ድኅነት ምክንያተ ድኅነት ድኅነት በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ የእምነትና የአምልኮ ቀኖና አፈጻጸም በብሉይና በሐዲስ ኪዳን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስትና እምነት የተከፈለ መሥዋዕትነት በዘመነ ሐዋርያት በዘመነ ሰማዕታት በዘመነ ሊቃውንት ነገረ ማርያምና ነገረ ቅዱሳን ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀት ምሥጢረ ሜሮን ምሥጢረ ቁርባን ምሥጢረ ክህነት ምሥጢረ ንስሐ ምሥጢረ ቀንዲል ምሥጢረ ተክሊል የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት ዘመነ መናፍቃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን አተካከልና አሠራር ሥርዓተ ጥምቀት ሥርዓተ ሜሮን ሥርዓተ ቁርባን ሥርዓተ ንስሐ ሥርዓተ ክህነት ሥርዓተ ተክሊል የስብከት ዘዴ ለሰባኪው የሚያስፈልገው የስብከት ዓይነቶች ስብከት የሚሰጥባቸው ቦታዎች ለተለያዩ ምእመናን የሚሰጡ ስብከቶች ስብከትና ፖለቲካ ስብከትና ኦርቶዶክሳዊ ጠባዩ በዕድሜ ደረጃ ከፋፍሎ ማስተማር በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምሳክ አሜን መግቢያ ለመንፈሳዊም ሆነ ለሥጋዊው ጥበብ መጻሕፍት ከፍ ያለ ድርሻ ያበረክታሉ ሰዎች ከበጎው የሚተባበሩበትን ከክፉው የሚርቁበትን የዕለት ተግቦራቸውን የሚያከናውኑበትን ምሥጢር ይገልጣሉ ያስረዳሉ በመሆኑም አንዳንድ የነገረ ሃይማኖት ሊቃውንት መጻሕፍትን «መንገድ አመልካቾች» በማለት ይጠሯቸዋል የጥንት አባቶቻችንም ይህን በመረዳት መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ የሚያስጨብጡ መጻሕፍትን በብዙ ድካም ብራና ፍቀውቀለም በጥብጠው ጽፈው አቆይተውልናል ይህም አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ያገኙትን ሃይማኖት ጥበብ እንድንይዝ አድርጎናል ቅደስት ቤተ ክርስቲያናችንንም የመጻሕፍት ማኅደር ለመሆን አስችሏታል መጽሐፍ ማዘጋጀት ብዙ ድካምና ውጣ ውረድ ያለበት ቢሆንም «በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል» እንዲሉ ሊቃውንት በጉባኤያቸው ያስተማሩት ትምርት ሳይጠፋ ሳይቆነጸል ለልጆቻቸው እንዲደርስ በማሰብ ጸሐፊ አዘጋጅተው አስጽፈው ለዛሬው ትውልድ አቆይተዋል አሁን ያሉ አባቶቻችንም ይህንኑ ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛሉ ማኅበረ ቅዱሳንም በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያናችን ያሏት ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜያት የሚያስተምሩት ትምህርት ለምእመናን እንዲዳረስ ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ በማለት መምህራን በቃል ያስተማሩትን በአንዳንድ ሽቶች ያሰፈሩትን በማሰባሰብ በመጻሕፍት መልክ እንዲቀርብ በማድረግ ላይ ይገኛል ይህ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት የተባለው መጽሐፍ ከላይ እንደተጠቀሰው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በካህናት ማሰልጠኛዎች በሰንበት ትቤቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መንፈሳዊ ጉባኤያት ያስተማሩት ትምህርት ውጤት ነው በዚህ መጽሐፍ የተካተቱት ትምህርቶች አብዛኞዎቹ በተለያዩ መምህራን በሽት መልክ የቀረቡ ነበሩ በመሆኑም ለአያያዝ የማይመቹ ለጉዳት የተጋለጡና ረጅም ጊዜ ለማቆየትና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የማይመቹ ናቸው ሽቶቹንም በጊዜው እያባዙ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረጉ ለከፍተኛ የገንዘብ የጊዜና የጉልበት መባከን የሚዳርጉ ናቸው እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የሊቃውንቱ ትምህርት በትምህርታቸው እንዲተላለፍና መጪው ትውልድ ቀደምት አባቶቹን በትምህርታቸው እንዲያውቅ ለማድረግ ትምህርቶቹን በጽሑፍ መልክ ማቅረቡ ታላቅ አስተዋጽዖ አለው ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ አድርጎ የተነሳው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ነገረ ሃይማኖትንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናቸውን ከማሳወቅ አንፃር ይህ መጽሐፍ ለተቋማቱ በማስተማርያነት መልክ የቀረበ ነው በመሆኑም በሁሉም ተቋማት በሚገኙ መንፈሳዋ ጉባኤያት መስጠት ያለበቸውን ትምህርቶች የካተተ በመሆኑ ተማሪዎቹ ተመርቀው ሲወጡ ስለ ነገረ ሃይማኖታቸው አንድ ዓይነት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል መጽሐፉ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና የስብከት ዘዴ የሚሉ ትምህርቶችን በውስጡ ያካተተ ነው በመጽሐፉ ውስጥ ከተካተቱ ትምህርቶች መካከል አንዳንዶቹ በሌሎች ሊቃውንት በመጽሐፍ መልክ የቀረቡ ቢሆንም በሁሉም ቦታ ያሉ ተማሪዎች የሚያገጃቸው በመሆኑና ለማስተማርያነትም ጉልህ ድርሻ ያሳቸው በመሆኑ በከፊል በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ሥልጠናዎች ተገኝተው በማሰልጠን ከመጻሕፍቶቻቸውም በከፊል ወስደን በዚህ መጽሐፍ አካተን እንድናሳትም የተባበሩንን መልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን የጠቤተ ክህነት ምዋና ሥራ አሥኪያጅ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ቀዳማዊ ሊቀካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየን በልዑል እግዚአብሔር ስም እናመሰግናቸዋለን በተለያዩ ቦታ የምትገኙ የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ውድና ብርቅ የሆኑ አባቶቻችን በብዙ ጥረትና ድካም አዘጋጅተዋቸው የቀሩትን ትምርቶች በማሰባሰብ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር የሚታተምበትንና ለትውልዱ አገልግሎት የሚሰጡበትን መንገድ እንድታመቻቹ አደራ እንላለን ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት በመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን የጠቤተ ክርህነት ምዋና ሥራ አሥኪያጅ መግቢያ «ወዘእንበለ ተአምኖሰ ኢይትከሃል ያሥምርዎ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም» ዕብ በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረው የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር ያለው ግንኙነት የአባትና ልጅ ያህል ወይም ከዚያ በላይ ቅርበት ያለው ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖርና እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚቻለውም በእምነት እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል ከዚያም በምን ዓይነት እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት እንደሚቻል ከራሱ ከቅዱስ መጽሐፍ ቃልና እንዲሁም ከዘመነ ብሉይና ከዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ምእመናን ሕይወት ሁሉንም ዓይነት ትምህርት ማግኘት ይቻላል የክርስትና እምነት የእግዚአብሔር ወዳጅነቱ ከተመሰከረለት ከአብርሃም እምነት የቀጠለ ትክክለኛ ሃይማኖት ስለሆነ በእምነትና በምግባር አብርሃምን መስሎና አህሎ በመኖር እግዚአብሔርን ማስደሰት የሚቻለው በዚህ እምነት ነው ለዚህ እምነት መሠረቱ ብሉይ ኪዳን ስለሆነ ትምህርተ «ክርስትናን» ከሥር መሠረቱ ጀምሮ መማር የሚቻለው ከብሉይ ኪዳን መነሣት ሲቻል ነው የክርስትና እምነት መሠረተ ትምህርት የሰው ልጅ ስለ እግዚአብሔር ኑባሬ ያለው ዕውቀት ፍጹምነት በመሠረቱ ዓለም በራሱ የተገኘና በራሱ የሚኖር ወይም ያለ አስገኝ በራሱ የተገኘና ያለሠራዒና መጋቢ በራሱ የሚኖር ሥነ ፍጥረት አይደለም ለተፈጥሮው አስገኝ ለኑሮው ሠራዒ መጋቢ ለጉዞው መነሻና መድረሻ አለው ከባሕር ወለል በላይ በተን መልክ ወደ አየር የወጣ ውኃ በዝናም መልክ ተመልሶ ወደ ምድር እንደሚወርድና ከዚያም ወንዝ ፈጥሮ ወደ ባሕር ወለል እንደሚጓዝ የሰው ልጅም እንዲሁ መነሻው መድረሻው የሆነ ተጓዥ እንደሆነ በቃለ እግዚአብሔር ምስክርነትና በእምነት ማወቅ ይቻላል የማያውቅም ይህን ሊያውቅ ይገባል ለዚህ ዕውቀትና እምነት ታዲያ ሥር መሠረቱ በቅድሚያ ለሚያየውም ሆነ የማይታየው ዓለም ፈጣሪና ሠራዒ መጋቢ እንደ አለው ማወቅና ማመን ነው የዕውቀት ምንጭ ሥነ ፍጥርት ስለ ሥነፍጥረት የሃይማኖት ትምህርት ቤትነት ማስረጃ ጥቅስ «ወዘሰ ኢያስተርኢ እግዚአብሔር እምፍጥረተ ዓለም ይትዐወቅ በፍጥረቱ ለፍጥረቱ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ እግዚአብሔር በፍጥረቱ ለፍጥረቱ ይታወቃል» ሮሜ «እንስሶችን ጠይቅ ያስተምሩሃል የሰማይንም ወፎች ጠይቅ ይነግሩሃል ወይም ለምድር ተናገር እስዋም ታስተምርሃለች የባሕርም ዓሦች ይነግሩሃል የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንደ አደረገ ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማነው። ኪዳነ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት ኪዳነ በረከት ማለት ነው ኪዳነ አዳም የሐዋ ገላ ኪዳነ አብርሃም የሐዋ ኪዳነ ኖኅ ዘፍ ዘመነ ተስፋ ከድቀተ አዳም እስከ ክርስቶስ ድረስ ያለው ዘመን የተስፋ ዘመን ይባላል ዘመነ ክርስትና ራሱ የትንሣኤ ሙታንና የመንግሥተ ሰማያት ተስፈኞች ዘመን እንደመሆኑ መጠን በእርግጥ የተስፋ ዘመን ሊባል ይችላል ሆኖም የአዲስ ኪዳን ሕዝብ የመንግሥተ ሰማያት ተስፈኛ ለመሆን የበቃው በክርስቶስ በተፈጸመው የድኅነተ ዓለም ተግባር ስለሆነ ዘመነ ተስፋ የሚለው ቃል ትክክለኛ መጠሪያ ሊሆን የሚችለው ከአዳም እስከ ክርስቶስ ለነበረው ዘመን ነው ኢትዮጵያዊው ደራሲ «ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል» ሲል የተናገረው ቃል የሚያረጋግጠውም ይህንኑ ሐቅ ነው ለዚህም የምስክርነት ቃል ምንጩ ቅዱስ መጽሐፍ መሆኑ ግልጽ ነው የሐዋ ገላ ወዘተ ዘመነ ተስፋና የዘመነ ተስፋ ኑሮ የተስፋ ዘመን «ዘመነ አበውና ዘመነ ኦሪት» በሚል ሁለት ክፍለ ዘመን ይከፈላል ሃይማኖተ አበውና ተስፋ አበው በጽኑዕ እምነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖትና ተስፋ ስለሆነ አምልኮተ እግዚአብሔር በሕገ ልቡና ይፈጸም በነበረበት በዚያ ዘመን እንኳ በዘመኑ ነዋሪዎች ላይ ይታይ የነበረው የእምነትና አምልኮ ጽናትና የምግባር ሥምረት ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ እለተ ምጽአት ለሚነ ምእመናን ሁሉ አብነትነት ያለው ሆኖ የሚኖር ነው ለምሳሌ የአቤል ምሥዋዕት ሥሙርነት ዘፍ ዕብ የሄኖክ እምነት አስደሳችነት ዘፍ ፅብ የኖኅ እምነት ተስፋ ፍጹምነት ዘፍ ዕብ ዕብ ያዕ ዘፍ የኢዮብ ትዕግሥት ዕፁብ ድንቅነት ያዕ የአብርሃም እምነትና ምግባር ፍጹምነት ዕብ ዘፍ የመልከ ጸዴቅ ክህነት አብነትነት ዘፍ ዕብ መዝ የሣራ ደግነት ዘፍ ጴጥ የርብቃ ትዳር ፈላጊነት ዘፍ በዘመነ ኦሪት ይፈጸም የነበረው የእምነትና አምልኮ ተግባር ከዘመነ አበው ጋር ሲነጻጸር በሕገ ልቡና ይፈጸም የነበረው ሥርዓተ አምልኮ በሕግ መጽሐፋዊና በሥዩማን ካህናት ሠራዒ መጋቢነት እንዲፈጸም ከመደረጉ በቀር የተቀነሰ ወይም የተጨመረ ነገረ ሃይማኖት የለም ድኅነትና ምሥጢረ ድኅነት «ድኅነት» የሚለው ቃል በአጭሩ የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ያጣውን የተፈጥሮ ጸጋ ክብር በአዲስ ተፈጥሮ እንደገና ለመታደል መብቃቱን ለመግለጽ የሚነገር ልዑል ቃል ነው በሌላም አገላለጽ ድኅነት የሚለው ቃል አዳም በክርስቶስ የታደለውን የሕይወተ ሥጋና ሕይወተ ነፍስ በረከተ ሥጋና በረከተ ነፍስ ጸጋ ሉቃ ሮሜ ወይም በሌላ አነጋገር የሞተ ሥጋና የሞተ ነፍስ ድቀት የደረሰበት አዳም በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘው የሐ ትንሣኤና ሕይወት የሚገለጽበት ሕያው ቃል ነው ዮሐ። በቀረበው ትንተና ላይ እንደሚታየው ይህ ምሥጢር በብዙ ዓይነት ገጸ ንባብ የተገለጠው የተለያየ ትርጉም ስላለው አይደለም ሁሉም ዓይነት ገጸ ንባብ ሲተረጐምና ሲመሠጠር የሚያስተላልፈው መልእክት አንድ ነው በሐዲስ ተፈጥሮ ወደ ጥንተ ተፈጥሮ ደረጃ መመለስ ከብልየት መታደስ በአዲስ ሕይወት የተፈጥሮ ጸጋን መልበስ ወዘተ ነው የድኅነተ ዓለም ተግባ ጸም እግዚአብሔር በኪዳነ አዳምና በኪዳነ አብርሃም ለሰው ልጅ የገባው ተስፋ ድኅነት የተፈጸመው በአንድ ልጁ ምሥጢረ ሥጋዌ ሲሆን ወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን የድኅነተ ዓለም ማቴ ተግባር የዲያብሎስና የፈጸመውም ሕማሙንና የሞት ድል መንሻ የኃጢአት መደምሰሻ ቆሮ ሞቱን ኢሳ የመንግሥተ ሰማያትና የዘለዓለማዊ ሕይወት መውረሻ ዮሐ ዕብ በማድረግ ነው የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን የፈቀደው ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ ሕይወትነት ሞተ ሥጋ በትንሣኤ ሥጋ ሞተ ነፍስ በሕይወተ ነፍስ ተደምስሷል የዚህ ድኅነት ባለቤት ለመሆን የሚቻለውም በትምህርተ ድኅነት ለሰው ልጅ ሊታደል የሚችልበትን ምሥጢር በመፈጸም የመድኃኒት ቤትነቷን በተግባር በመተርጎም ላይ ትገኛለች እግዚአብሔር «የድኅነት አምላክ» ተብሎ የሚጠራው በልጁ ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በፈጸመው የድኅነተ ዓለም ተግባር ብቻ አይደለም በኪዳነ ኖኅ ዘፍ እንደተገለጠው ከዚያም በፊት ለሰው ልጅ ኑሮ ደኅንነት ይፈጽመው በነበረ የትድግና ተግባር የድኅነት አምላክ መሆኑን ለሰው ልጅ በተግባር ገልጂል ይህንንም ከሚከተለው ትንተና መረዳት ይቻላል ድኅነት ምሥጢረ ድኅነትና ምክንያተ ድኅነት በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ የዘመነ ብሉይ ድኅነትና ምክንያተ ድኅነት ድኅነት ምክንያተ ደኀነት በዚህ ዓለም ላይ ለመኖር የሚቻልበትን ምክንያት ሁሉ ከሚያሳጣ አባር ቸነፈር ኢዮ ስደትና ምርኮ ኤር የነፃነት እጦትና የባዕድ ተገዥነት በጸምነትዛ ክምስኮ ጸክካሄዶገ ከክግዚክብሔር ጋር ማቋረግ ስብ ዩምነትና ክምስኮ መሥዋስሰት ጸቅርቦት ዘፍ ኪዮ ጸሎትና ጾም ሻ ነገ ዮና ዚ ምጽዋት ጻገ ክገግዳ ተቀባርጾነት ዘፍ ሸግዚጸብሔር ክገደፈጣዕነተቱና ክምሳክነቱ የሚፀደርገው ኤር ዘፀ ወዘተ አደጋ በእግዚአብሔር ረድኤት በመጠበቅ የሕይወት ኑሮ መኖር ቸርነት መዝ የዘመነ ሐዲስ ድኅነትና ምክንያተ ድኅነት ድኅነት ምክንያተ ድኅነት በአዲስ ተፈጥሮ ወደ ጥንተ ተፈጥሮ ደረጃ መመለስ ቆቁሮ ኤፌ በጥምቀት እንደገና መወለድ ዮሐ « ከኃጢአት ባርነት ነፃ መውጣት ዮሐ ከማዕሰረ ኃጢአት መፈታት ዮሐ ሞተ ሥጋንና ሞተ ነፍስን በትንሣኤና ሕይወት ድል መንሣት ዮሐ ቆሮ « ከኃጢአት እድፈት መንጻት ዕብ ራፅዕ በምድራዊና ሰማያዊ በረከት መባረክ ዮሐ የክርስትና ክምነትና ጥምቀት ማር ምግባር ስ ማቴ ምሥጢረ ቁዌቁርባኘን መኗጸም ዮጠሐ ኳቅር ጸጥ ጾም ጸሱትና ገስሐ የሐዋ የሐዋ ፎወቅርታ ማድረግ ማቴ ምጽዋት ማቴ ዩቅዱሳገ ስማሳጅነትና በስማቸው የሚፈጸም ምግባረ ሠባ ማቴ የሸግዚስብሔር ቸርነት ርሜፋ የክርስቶስ ማንነት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ለክርስትና እምነት መሠረቱ ይህ ዕውቀት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር እንደሆነ ማወቅ ሕይወት ያለው ዕውቀት ነው ዮሐ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችውም በዚህ እምነት ላይ ነው ማቴ ያለዚህ እምነት በኑዕ ዐለት ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ባለቤት መሆን አይቻልም የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው በዚህ ሥጋዌ ኃጢአተኛውን ዓለም ለማዳን አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ነው ኤፌ ፅዝራ ሱቱኤል ከእግዚአብሔር ጋር ቃል በቃል ለመነጋገር በበቃበት የራእይ ወቅት እግዚአብሔር ዓለምን በማን ሊጎበኝ እንዳሰበ ለመጠየቅ መቻሉንና ከዚያም በመልሱ ጎብኙ ራሱ መሆኑንና ይህን ጉብኝት ለማድረግ ፈቃዱ የሆነውም ከፍጥረተ ዓለም በፊት ጀምሮ እንደነበር ለመረዳት እንደቻለ በስሙ የተጻፈው መጽሐፍ ቃል ያረጋግጣል ዕዝራሱቱኤል ይህም የሚያመለክተው የክርስቶስ ምጽአት ከጊዜ በኋላ ታስቦ የተፈጸመ ድርጊት አለመሆኑን ነው ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ ምሥጢረ ምጽአቱን አስቀድሞ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት ተፀነሰ ተወለደ ቀስ በቀስ አደገ በሠላሳ ዘመኑ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ በመጠመቅ የእኛን ጥምቀት ባረከ ከዚያም በምድር ላይ በመመላለስ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበከ አስተማረ ስለእኛ ስለሰዎችና ስለመዳናችን በመስቀል ላይ ተሰቀለ ሞተ በሦሰተኛው ቀን ተነሣ በአርባኛው ቀን አረገ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ላከ ዳግመኛ ለፍርድ እንደሚመጣም በሐዲስ ኪዳን ፍጹም ተስፋ ሰጠ የእምነትና አምልኮ ቀኖና አፈጻጸም በብሉይና ሐዲስ ኪዳን በዘመነ ብሉይ በዘመነ አበው በዘመነ ኦሪት ቀደም ብሎ በተጠቀሰው መንገድ ከፈጣሪ ጋር ግንኙነት በማድረግና የሚፈለገውንም መሪ ቃል በመቀበል የአምልኮ ግዴታን በሕገ ልቡና መፈጸም በኪዳነ አብርሃም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የገባው ቃል ኪዳን የሚጠይቀውን ግዴታ በመፈጸም የአብርሃማዊ በረከት ተጠቃሚ መሆን ዘጸ የቃል ኪዳን ግዴታ ጽድቅና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ መጠበቅ ዘፍ የአማናዊ ጥምቀት ምሳሌ የሆነውን ሥርዓተ ምሳሌ የሆነውን ሥርዓተ ግዝረት መፈጸም ዘፍ የአብርሃምን እምነትና ምግባር ግዴታ በሕግ መጽሐፋዊ መፈጸም ዘሌ ዘጸ ሥርዓተ ግዝረትን መፈጸም ዘሌ የአምልኮ መሥዋዕት በማቅረብ በረከትን የኃጢአት ሥርየትን የአረቦን ድኅነትን ወዘተ ለማግኘት መብቃት ዕብ በጸሎት አቅርቦት አምልኮትን በመግለጽ የራስንም ሆነ የሌላውን ደኅንነት ማስጠበቅ ነገ ዘፀ ዘጉ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከዘመነ አበው ቅዱሳን ምእመን የእነሄኖከን አብርሃምን ይስሐቅንና ያዕቆብን ከዘመነ ኦሪት የእነሙሴን ጌዴዎንን ባርቅን ሶሞሶንን ዮፍታሔን ስም በመጠቃቀስ ስለ የአምልኮ መሥዋዕት በማቅረብና በእምነት እምነታቸው ደግነት በምሳሌነት ያወሳል የእግዚአብሔርን ስም በመጥራት የአብርሃም ዕብ በረከት ተሳታፊ መሆን ዘፍ በጸሎት አቅርቦት አምልኮትን መግለጽ ኢዮብ ኢዮ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሥጢረ ሥላሴ ምሥጢረ ሥላሴ እግዚአብሔር አንድ ነው ነገር ግን ሦስት ገጽ ሦስት አካል አሉት እነዚህም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው አብ አባት ነው ወልድ ልጅ ነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሠረጸ ነው ሦስት አካላት አንድ መለኮት ናቸው ምሥጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን ብዙ ጐልቶ ባይነገርም አልፎ አልፎ በሥነ ፍጥረትና በነቢያትም ታውቋል ዘፍጥ ኢሳ በሐዲስ ኪዳን ግን በምሥጢረ ሥጋዌ ምሥጢረ ሥላሴ በሚገባ ታውቋል በዮርዳኖስ በደብረ ታቦር ማቴ በሊቃውንትም ዘንድ በምሥጢረ ሥላሴ የአብ ወላዲነት የወልድ ተወላዲነትና የመንፈስ ቅዱስም ከአብ መሥረጽ በሰፊው ተተርጉሟል አብ ወላዲ ነው ወልድ ተወላዲ ነው መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ ነው አብ ተወላዲ አይባልም ወልድ ወላዲ አይባልምመንፈስ ቅዱስ ወላዲ ተወላዲ አይባልም ወላዲተወላዲሠራጺ የሚባሉት ቃላት ሦስቱ አካላት ለየብቻ የሚታወቁባቸው የግብር ስሞች ናቸው። አባላቱ ወደ ተለያዩ አኅጉር ስለተሰደዱ ኢየሩሳሌም ሳይ አንደ ኩሬ ውኃ በአንድ ቦታ ተገድቦ የነበረው የክርስትና እምነት ትምህርት እንደ መስኖ ውኃ በየአህጉሩ ተሰራጨ በተለይ ወደ አንጾኪያ ተሰድደው የነበሩት ክርስቲያኖች አንድነት እየጠነከረ ስለሄደ «ደቀ መዛሙርት ናዝራውያን» የሐዋ እየተባሉ ይጠሩ የነበሩት ምእመናን «ክርስቲያን» ተብለው ተሰየሙ የሐዋራ የክርስትና እምነት በዓለም ላይ ያደረገውን መስፋፋትና መጠናከር በምሳሌ መግለጽ ቢያስፈልግ ትክክለኛ ተነጻጻሪ ሆኖ የሚገኘው በቅዱስ ወንጌል እንደተገለጠው የሰናፍጭ ዘር ነው የሰናፍጭ ቅንጣት እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነች የዘር ዓይነት ናት ሆኖም ከእርሻ ላይ ስትዘራ የወፎች ማረፊያ የሆነች የዘር ዓይነት ናት ሆኖም ከእርሻ ላይ ስትዘራ የወፎች ማረፊያ ለመሆን እስከምትችል ድረስ ታላቅ ዛፍ ትሆናለች ማቴ የቤተ ክርስቲያንም የዕድገት ልክ እንደዚህ ነው የተነሣችበትንና የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ ዝቅታና ከፍታ ያለማብራሪያ ከምሳሌው መረዳት ይቻላል ሆኖም ቤተ ክርስቲያን ይህን ስፋት ያላት ታላቅ የሕይወት ዛፍ የሆነችው በዝናም ውኃ አይደለም የወንጌል ጠለ ትምህርት የማይለያት የክርስቶስ ተክል ስለሆነች ነው ቃለ ወንጌል በተዘራበት ቦታ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ትበቅላለች ዘሪው ጴጥሮስም ይሁን ጳውሎስ ወይም ሌላ የተዘራው ዘር የሚበቅለውና የሚያድገው በእግዚአብሔር አምላካዊ ግብር ነው ቆሮ ማር ምድር እንኳ ጠቃሚ ፍሬን የምትሰጠው ከላይ በእርሷ ላይ የሚወርደው የዝናም ነጠብጣብ ብቻ አይደለም በሁሉም ወራት የምሕረት ዝናምን ከሚለግሳት እግዚአብሔር የተዘራው ለመብቀል የበቀለው ለማደግና ፍሬ ለመስጠት የሚበቃበትን በረከት ስታገኝ ነው ዕብ የተዘራው የሚበቅለው የተተከለው የሚጸድቀው በግብር አምላካዊ እንደሆነ ቢታመንም ለምድራዊው የግብርና ተግባር ትጉህ ገበሬ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለሰማያዊው ግብርናም እንዲሁ ከዚያ የላቀ ትጉህ ታጋሽና ጠንካራ የወንጌል ገበሬ ያስፈልጋል የግብርና ትልቁ ተግባር ደግሞ የተዘራውን ሰብል ከአረምና ከተባይ ተጠ ቂነት መጠበቅ ነው ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ መረዳት የሚቻለውም የወንጌል ገበሬዎችንና የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎችን ከፍተኛ ተልዕኮ የጠየቀው ቃለ እግዚአብሔርን ወይም ቃለ ወንጌልን የመዝራቱ ተግባር ብቻ ሳይሆን የተዘራውን ቃለ እግዚአብሔር ከሰው ሠራሽ አረምና ተባይ ኑፋቄ ጥቃት የመጠበቁ ተግባር ነበር በመሆኑም ከውጭና ከውስጥ የሚያጋጥመውን ፈተና ለመቋቋም ብዙ ደም ፈስሷል ብዙ ገድል ተፈጽሟል ብዙ መሥዋዕትነት ተከፍላል ስለ ክርስትና እምነትና ሕይወት የተከፈለ መሥዋዕትነት በዘመነ ሐዋርያት ዘመነ ሰማዕታትና ዘመነ ሊቃውንት ዘመነ ሐዋርያት «የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል እንግዲህ ያላመነበትን እንዴት ይጠሩታል ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደተጻፈ ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ» ሮሜ ዘመነ ሐዋርያት የክርስትና እምነት የዓለም ሃይማኖት ለመሆን የበቃበት ሐዋርያዊ ጉዞ በመንፈስ ቅዱስ ተባርኮ የተጀመረበት በጉዞው ውጤታማነት የሐዋርያት የዓለም ጨውነት የዓለም ብርሃንነት የተረጋገጠበት ዓለም በጥበቡ ሊደርስበት ያልቻለው የድኅነተ ዓለም ምሥጢር በስብከተ ወንጌል ሥርጭት ገሃድ የሆነበት ቆሮ የቃለ ወንጌል ዘርና መከር ወቅት ነው ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ከታጠቁ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ሂዱና አስተምሩ ማቴሾ በጨለማ የነገረኳችሁን በብርሃን ተናገሩት በጆሮአችሁ በሹክሹክታ የነገርኋችሁን በሰገነት ላይ ስበኩት ማቴ ሲል የሰጣቸውን ትእዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ዓለም ወጡ መልካሙን የምሥራች ዜና አወሩ የሕይወትንም ቃል ለዓለም አሰሙ የዓለምን ጨለማ ለማራቅና አልጫውን ዓለም ለማጣፈጥ የሚቻልበትን የብርሃንነትና የጨውነት ተግባር ፈጸሙ የተኛውን ቀሰቀሱ የሞተውን አስነሠ ኤፌ የነቃውም ዓለም የተነገረውን የምሥራች ቃል ሰማይድንበተ የነበረውነ ስም ተቀብሉ በክርስትና እምነት ተጠራ የሐዋ ቃለ ወንጌል በዚህ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ሳይ የተዘራውና ይህ የሕይወት ፍሬ የተመሠረተው እንግዲህ በእነዚህ ሐዋርያት የወንጌል ግብርና ስለሆነ ዘመነ ሐዋርያት ለክርስትና እምነት በእርግጥ ዘመነ ዘርና ዘመነ ፍሬ እንደሆነ በግልጽ ይታያል ይህ እንዲህ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በዚያ የበረከት ዘመን እንደ ሲሞን መሠርይ ያሉ የሐዋ ቢጽ ሐሳውያን ወይም መናፍቃን ከውስጥም ከውጭም በመነሣት የክርስትና እምነትን ለመበረዝ ለማደስና ለመለወጥ ያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ቀላል ስላልነበረ ዘመኑ የፈተና ዘመን እንደነበረ ማወቅ ይቻላል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ «እኛ ከሰበክንላችሁ ወንግል የሚለይ ትምህርትን ከሰማይ መልአክ እንኳ ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን» ገሳ ሲል በመረረ ቃል ያስጠነቀቀውም ስለዚህ ነበር ዘመነ ሰማዕታት ዘመነ ሰማዕታት የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትነው የእምነታቸውን ደግነት በተግባር ያረጋገጡበት የገድልና ትሩፋት ዘመን ነው ቤተ ክርስቲያን የዚህ ገድል ፈጻሚ መሆን የጀመረችውም ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ መሆኑ አይካድም ለምሳሌ በሐዋርያነት ከተሾሙት ሰባት ዲያቆናት አንዱ የነበረው እስጢፋኖስ በክርስትና እምነት ተቃዋሚዎች በድንጋይ ተደብድቦ የሰማዕትነትን ገድል የፈጸመው በዘመነ ሐዋርያት ነው የሐዋ ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቀዳሜ ሰማዕት ተብሎ ለመጠራት የበቃውም በዚህ ምክንያት ነው ቀጥሎም ሐዋርያው ያዕቆብ በአረማዊው ሄሮድስ ትእዛዝ በሰይፍ ተሰይፎ የሰማዕትነትን ጽዋ የተቀበለው በዚያ ዘመን መሆኑ ግልጽ ነው የሐዋራ ነገሩ እንዲህ ሲሆን ታዲያ ዘመነ ሰማዕታት ከዘመነ ሐዋርያት የተለየ ክፍለ ዘመን እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድ የቻለው በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ አጠቃላይ ጥፋት አዋጅ ለታወጀበትና አዋጁ ተግባራዊ ለሆነበት ልዩ የሥቃይ ወቅት ይህ ስያሜ እንዲሰጠው ስለተደረገ ነው ለዚህ ኢሰብአዊ አዋጅ የታሪክ ተጠያቂ የሆነውም ሮማዊው ቄሣር ዲዮቅልጥያኖስ ነው ሆኖም ድርጊቱ በሰላም ዘመን ሊፈጠሩ የማይችሉ አያሌ ሰማዕታት መገኘት ምክንያት ከመሆኑ በቀር በክርስትና እምነት ሂደት ላይ የፈጠረው መሰናክል አልነበረም አስቀድሞ እንደተገለጠው ይህ ዕልቂት በይበልጥ ተግባራዊ የሆነው ከ እኤትአ ወይም ከ እኤአ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ስለሆነ ይህ ወቅት ዓመተ ሰማዕታት በመባል ለሚታወቀው የዘመን አቆጣጠር የታወቀ መነሻ ሆኖ ይገኛል ይህ ሁሉ የሚያመለክተው የክርስትና እምነት ምን ያህል መሥዋዕትነት የተከፈለበት ሃይማኖት መሆኑን ነው ዘመነ ሊቃውንት ዘመነ ሊቃውንት በክርስቶስ የተነገረውና በሐዋርያት የተሰበከው ቃለ ወንጌልም ሆነ የድኅነተ ዓለም ተግባር አፈጻጸም በስፋትና በጥልቀት የተመሠጠረበት የነገረ ሃይማኖት ቀኖና በዓለም አቀፍ ጉባኤ የተደነገገበትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት መልክና ቅርጽ እንዲኖረው የተደረገበት ሌላው የቤተ ክርስቲያን ወርቃማ ዘመን ነው ይህ እንዲህ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ዘመን የመናፍቃን መፍለቂያ ዘመን በመሆኑ ሌላው ዘመነ ሰማዕታት መሆኑ አልቀረም። ሆኖም የክርስትና እምነት በየጊዜው የሐዋርያትን የሰማዕታትን የሊቃውንትን የመናንያንን መኖር የሚጠይቅ የገድልና ትሩፋት እምነት ስለሆነ ዘመነ ሐዋርያት ዘመነ ሰማዕታት ዘመነ ሊቃውንት ዘመነ ጻድቃን መናንያን መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ ያለው ዘመን አይደለም በዚህ ትረካ ለመጠ ቆም የተፈለገውም መጀመሪያውን እንጂ መጨረሻውን አይደለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ ሁኑ» ማቴ ሲል እንደተናገረው ሁሉንም ዓይነት ገድል መፈጸም የሚቻለው ደግሞ የትኛውም ጊዜ የሚጠይቀውን ጥበብ ከየዋህነት ጋር በመላበስ እንጂ ከእነዚህ ነገሮች ባዶ በሆነ ሰውነት አይደለም ነገረ ማርያምና ነገረ ቅዱሳን ሀ ነገረ ማርያም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በንጽሕና በቅድስና በሞገስና በጸጋ በክብር የሚመስላትም ሆነ የሚያህላት የሌለ እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የያዘች ከሆነ ጀምሮ በአዳም ልጅነቷ ምክንያት ንጽሐ ጠባይ ያላደፈባት በዚህ ዓለም ኑሮዋም ከሀልዮ ከነቢብና ከገቢር ኃጢአት ንጽሕት የሆነች ከቅዱሳን ሁሉ በላይ ጸጋን የተሞላች ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች በአማላጅነቷ የምእመናን ሁሉ መማጸኛ የሆነች የአምላክ እናት ናት ሉቃሕዝመኃመዝ ኢሳ ስለ ንጽሕናዋ ቴዎዶጦስ ሃይአበም ስለ ክብሯ ታላቅነት ዮሐንስ አፈወርቅ ሃይአበም እና ሌሎችም አበው የተናገሩትን ይመለከቷል በዚህ ምክንያት ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ ምልዕተ ጸጋ ምልዕተ ክብር እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እመ እግዚአብሔር ሰአሊተ ምሕረት ድንግል በክልኤ ቅድስተ ቅዱሳን መትሕተ ፈጣሪ መልእልተ ፍጡራን ወዘተ እየተባለች ትጠራለች ለዚህም ምንጩ የወንጌል ውዳሴ ማርያም ነው ሉቃራ ዮሐ ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ የታወቀው የቅዳሴ ማርያም ደራሲ አባ ሕርያቆስ «ወስሉጥ ስመኪ በኀበ እግዚአብሔር» ሲል እንደተናገረው የኢትዮትያ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን የተሰጠ ው ቃል ኪዳንና ክብር ከሁሉም ቅዱሳን በላይ መሆኑን ታምናለች ታስተምራለች በመሆኑም በማንኛውም ጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ስሟ በተማኅጽኖ ይጠራል ከዚህም ጋር በኢትዮጵያም ሆነ በሌላው የክርስትና ዓለም በጸሎትም ሆነ በትምህርት ስሟ ሳይጠራ የሚውልበት ዕለት የለም ለ ነገረ ቅዱሳን መላእክት አበው ነቢያት ሐዋርያት ሰማዕታት ጻድቃን በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ ዘሌ ጴጥ ዮሐ ለ የቅዱሳን መላእክት አገልግሉት ስለሰው ልጅ ሕይወት መላላክ ዕብ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ማመስገን ራእ የሰውን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ማድረስ ለሰው ልጅ ምሕረት መለመን ዳን ሉቃ ዮሐ የሰውን ነፍስ ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ መሱቱ ፍጥረተ ዓለምን የሰውን ልጅ መጠበቅ ማቴ ዳንራ ለምሕረትም ለመዓትም መላክ ሮሜ በመከራና በችግር ጊዜ ለተራዳኢነት መላክ ዮሐ በፍጻሜ ዘመን ኃጥአንን ከጻድቃን መለየት ማቴ ራዕ ለ የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ ጸሎታቸውም ምኞታቸውም ደስታቸውም የሰው ልጅ ድኅነት ነው ዘፍ ዳን ሉቃ ይሁዳ ዘካ ዘጸሩ መዝ ለ ክብረ ቅዱሳን መላእክት ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከበሩና ባለሟልነትንም ያገኙ ቅዱሳን በመሆናቸው በሰውም ዘንድ የተከበሩ ናቸው ስለሆነም የአክብሮት ስግደት ይሰገድላቸዋል በስማቸው ቤተ ክርስቲያን እንዲታነጽም ይደረጋል ዳን ዘፍ ዘጉ ኢያ ለ ስለ ቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት ሰማዕታት ጻድቃን ክብር እነዚህ ቅዱሳን የየራሳቸው ተልዕኮ በገድል በትሩፋት የፈጸሙ ቅዱሳንና ቅዱሳት በመሆናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ ክብር አላቸው የቃል ኪዳን ቅዱሳን በመሆናቸውም ምእመናንን በስማቸው ወደ እግዚአብሔር ይማጸናሉ እነርሱም በዐጸደ ነፍስ ይማልዳሉ ማቴ ዘጸ ሄኖክፊ በነፍስ ሕያዋን ስለሆኑ ሉቃ በዚህ ምክንያት የአክብሮት ስግደት ይሰገድላቸዋል እግዚአብሔር የሚወዳቸውና የሚያከብራቸው ስለሆኑ ራሆ ማጠቃለያ የሃይማኖት ትምህርት ፍሬውጤቱ የእምነት የተስፋ የፍቅር ፍጹምነት ስለሆነ ይህ ውጤት የማይታይ ከሆነ ትምህርቱ በመልካም ምድር ላይ የወደቀ ዘር አልሆነም በኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡና ሳይ የወደቀው ቃለ እግዚአብሔር በመልካም ምድር ላይ የወደቀ ዘር ስለሆነ ፍሬው እነሆ የተትረፈረፈ ሆኖ ይታያል ሆኖም ባማረው የስንዴ ማሳ ላይ እንክርዳድ እንዳይዘራበት ንቁና ትጉኅ የወንጌል ገበሬ ሆኖ መኖር ከቤተ ክርስተያኒቱ የሃይማኖት መምህራን የሚጠበቅ ግዴታ ይሆናል ይህም ምን ጊዜም ቸል ሊባል የማይገባው ኃላፊነት ነው ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact